መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ጽጌ ቅድስ ኡራኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ኃይል ራጉኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/590538kidste_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/895720giorgis.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/903816bole_medhaniealem.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/683566trinity.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/821897entoto_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/310283meskaye_1.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/904160BEATA_MARIAM.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/578084urael.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/812647gebrie_gedam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/681179raguel.jpg
መምህር ጎይቶኦም ያይኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ!!

2g23

መምህር ጎይቶኦም ያይኑ የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዥን ፕሮግራም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን እና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነትን በተመለከተ የተለየ አደረጃጀት የለውም፤ የምንሠራው ቤተ ክርስቲያን ባስቀመጠችው አሠራር ነው፤ በቃለ ዓዋዲው መሠረት ሀገረ ስብከቱ የተለያዩ ክፍሎች አሉት፤ የሁሉም ክፍሎች በተሣካ አደረጃጅ ተደራጅተዋል፡፡
በየክፍሉ ንዑሳን ክፍሎች አሉ፤ አዲስ አበባ ከተማ በክፍላተ ከተማ አወቃቀር አስር ክፍላተ ከተማ ነው ያለው፤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሥር ግን የተዋቀሩት የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሰባት ክፍላተ ከተማ  ናቸው፤ የአንዱ ክፍለ ከተማ መዋቅር ሦስት ክፍለ ከተሞች ጠቅልሎ የያዘ ነው፤
 ለምሳሌ አዲስ ክፍለ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማና ልደታ ክፍለ ከተማ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር እንደ አንድ ክፍለ ከተማ ይቆጠራል፤  በዚህ መሠረት በሀገረ ስብከቱ ሥር ሰባት ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት አሉን ማለት ነው፡፡
በሌላው ሀገረ ስብከት እንደሚታወቀው ከሀገረ ስብከቱ ቀጥሎ ያለው ወረዳ ቤተ ክህነት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ደረጃ ግን ወረዳ ቤተ ክህነት የሚል ክፍል የለም፡፡ የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ነው የሚባለው፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ያሉት ገዳማትና አድባራት ብዛት እስከ 2008 ዓ.ም የበጀት ዓመት ድረስ 180 ነበር፤ በዚህ ዓመት የገዳማትና አድባራት ብዛት በጠቅላላ 198 ደርሷል፡፡
በዚህ በዓቢይ ጾም ውስጥ የሚካሄደውን መንፈሳዊ አገልግሎት በተመለከተ እንደማንኛውም ጊዜ ተመሳሳይ ቢሆንም እንኳን በክርስቶስ የተመሠረተችው ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብክ የታወቀ ሲሆን በቀኖናዋ መሠረት እያገለገለች ትገኛለች፡፡
የሀገረ ስብከቱ ሥራ በተሻለ መጠን ለምዕመናን ብቁ አገልግሎት በማጠናከር ከሌላው ጊዜ በጾሙ ወራት ምዕመናን ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ አምልኮታቸውን በአግባቡ እንዲፈጽሙ፣ በተለይ በስብከተ ወንጌል ደረጃ ለየት ያለ በገዳማቱና በአድባራቱ የአንድነት መርሐ ግብር አለ፡፡
ስለዚህ አንድነት ጉባኤው ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ሰፊ የሆነ እንቅስቃሴና የተጠናከረ ክትትል እያደረግን ነው ያለ ነው፡፡ በሀገረ ስብከት ደረጃ ብቻ ሳይሆን እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ከምን ጊዜም በበለጠ ክትትልና ቁጥጥር ያለው የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር፣ በጸሎተ ምሕላም፣ በስብከተ ወንጌልም፣ በሥርዓቱና በቀኖናው መሠረት እንዲካሄድ እየተደረገ ነው፡፡ አዳዲስ በተተከሉ አብያተ ክርስቲያናትም ጭምር ሥርዓተ አምልኮው ወይም የሱባኤው መርሐ ግብር በተጠናከረ መልኩ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፤ በሁሉም ገዳማትና አድባራት የስብከተ ወንጌል መምህራን ተመድበዋል፡፡
እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው አደጋ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አደጋ ምክንያት የተለየ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ ለሰባት ቀናት ያህል ጸሎተ ምሕላና ጸሎተ ፍትሓት እንዲደረግ በተላለፈው መመሪያ መሠረት በገዳማቱና በአድባራቱ ሥርዓቱ እንዲደርስ ተደርጓል፤ በአደጋው የሞቱትን ወገኖቻችንን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በገነት እንዲአኖርልን እና እረፍተ ነፍስ እዲሰጥልን በሁሉም ገዳማትና አድባራት ምህላው በአግባቡ እየተካሄደ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡
በአደጋው ወደ ተጎዱት ወገኖቻችን በአካል በመሄድ ለማጽናናት ችለናል፤ አሁንም ቢሆን ገዳማቱና አድባራቱ አስተዋፅኦ እንዲአደርጉ ሰፊ የሆነ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው የሚገኘው፤  እንደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለተጎዱት ወገኖች በአዲስ አበባ መስተዳደር በተቋቋመው ኮሚቴ በኩል አንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፤ ይህ አሠራር በሁሉም አጥቢያዎች ይቀጥላል፤ እንኳንስ ወገኖቻችንን ቀርቶ ማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር መርዳት አለብን፡፡
የተለያዩ ኮሚቴዎችም ተዋቅረዋል፤ በዚሁ መሠረት በየጊዜው ክትትል እያደረግን የተሻለ ሥራ ለመሥራት እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን፤ ወቅቱ የሱባኤና የጾም ጊዜ በመሆኑ ገዳማትና አድባራት በሥራቸው ያሉ አገልጋዮች፣ እንደዚሁም በየአጥቢያው ያሉ ምዕመናን ሱባኤውን ምክንያት በማድረግ በተለየ መልኩ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ስለሚገባቸው የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁላችንም ጥረት ማድረግ አለብን፤ በጾም ጊዜ ሲባልም ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ተለይቶ ይኖራል ማለት አይደለም፡፡
ነገር ግን ሱባኤ ሲሆን በተለየ መልኩ ከሌላው ጊዜ የተሻለ ጊዜና የተሻለ ሁኔታ በመፍጠር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን ለማለት ነው፡፡
ስለዚህ ምዕመናን በተረጋጋና በሰላም ሥርዓተ አምልኮታቸውን እንዲፈጽሙ ስብከተ ወንጌል በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ቁጥጥርና ትጋት ያስፈልጋል፡፡ በልማቱም ዘርፍ ቢሆን የተሻለ ልማት እንዲኖር የሁላችንም ጥረት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ምዕመናን የሚሰጡትን ገንዘብ በአግባቡ በመሰብሰብ ቤተ ክርስቲያን በአግባቡ እንድትለማ፣ ወቅቱ የሚጠብቀውን ሥራ ለመሥራት እስከ አሁን ድረስ አባቶቻችን ይህችን ቤተ ክርስቲያን በአግባቡ ጠብቀው አቆይተውልናል፤ እኛም ደግሞ እግዚአብሔር ፈቅዶ እዚህ ጊዜ ደርሰናል፡፡
ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን የሚሆን ወቅቱ የሚጠይቀው ሥራ ለመሥራት የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለብን፡፡
መምህር ጎይቶኦም ያይኑ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ
 

 
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለ130 ገዳማትና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች 3ኛ ዙር ዘመናዊ የሒሳብ አያያዝ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

0127

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ130 ገዳማትና አድባራት ለተወጣጡ የሒሳብ ሠራተኞችና ከሰባቱም ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ለተውጣጡ 14 ሠራተኞች በዘመናዊ የሒሳብ አያያዝ ሙያ ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተገጿል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ  ባለሙያዎችና ከሌሎች ተቋማት የተጋበዙ የሒሳብ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ የስልጠናው ጊዜ ከመጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
ሰልጣኖቹ ስልጠናውን የሚወስዱት በቲኦሪ እና በተግባር ላይ በተመሠረተ አሠራር ነው፡፡ ሠልጣኞቹ ከብዛታቸው አንፃር የተነሣ በ3 ቡድን ተከፋፍለው ሁለቱ ቡድን በ4 ኪሎ በሚገኘው በሲፒዩ ኮሌጅ በኮምፒውተር (በተግባር) ስልጠናውን ሲወስዱ አንደኛው ቡድን ደግሞ በሀገረ ስብከቱ የሥልጠኛ ማዕከል በኮምፒውተር (በተግባር) እየወሰዱ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ 
ለስልጠናው በተዘጋጀው የመማሪያ ዝግጅት ላይ በተብራራው መሠረት የሒሳብ አያያዝ ትርጉምና ታሪካዊ አመጣጡ፣ የዓላማችን የንግድ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት እያጎላው የመጣ መሆኑ፣ የመንትያ ሒሳብ (double entry) አመዘጋገብ  ሲስተም ለሒሳብ አያያዝ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ፣ የሒሳብ አያያዝ ማለት ገንዘብ፣ ቋሚና አላቂ ንብረት መረጃዎች የሒሳብ አያያዝ መሆናችን መሠረት ያደረገ መሆኑ፣ በአይነታቸው በማደራጀት፣ በመተንተን ለግምገማና ውሳኔ አሰጣጥ በሚያመች  በሪፖርት የመግለፅ ሂደት፣ በሒሳብ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱ የሒሳብ መረጃዎች፣ ቋሚ ንብረቶች የተገዙበትን ዋጋና አሁን ያላቸውን የመዝገብ ዋጋ ማሳየት፣ ሀብትና እዳን ለይቶ ማወቅ፣ በየቀኑ የተገኘውን ገቢና ወጪውን ከምክንያት ጋር ማያያዝ፣ የተገዙና የተሸጡ  ዕቃዎችን አገልግሎት መለየት፣ የሽያጩ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመጋዘን የተከማቹ የንግድ ዕቃዎች አይነት ብዛትና ለዕቃዎች የተደረገውን ወጪ እንዲሁም ዕቃዎቹ የተገመቱበት ዘዴ፣ በሒሳብ ዘመኑ መጨረሻ በዕዳ ያሉትን ዕቃዎች ማሳየት፣ የግብር ዓመት፣ በባንክ እና በእጅ ምን ያህል ጥሬ ገንዘብ እንዳለ ማወቅ፣ ያልተሰበሰበ ገቢና ያልተከፈለ ዕዳን በመዝገብ ላይ የተመሠረተ የሒሳብ አያያዝ፣ የነጠላና ጥንድ (Single entry) (Double entry)፣ የገቢ ማሰባሰቢያ ደረሰኞች፣ የንብረት መቀበያ ደረሰኞች የሚሉት የሥልጠናው ቁልፍ ሐሳቦች ሲሆኑ ሠልጣኞቹ በጋራ የተማሩአቸውን የሒሳብ መርሆች በመጀመሪያ በቲኦሪ ከተማሩ በኋላ  እንደገና በግሩፕ እና በግል በመሥራት ተግባር ተኮር ሥልጠና ወስደዋል፡፡
ይህ ዘመናዊ የሒሳብ አያያዝ ሙያ ስልጠና ባለፈው ዓመት እስከ 2ኛ ዙር የተሠጠ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት ደግሞ በአይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ስልጠና ለ3ኛ ዙር የተሰጠ እና የመጨረሻ የስልጠና ሂደት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የሰለጠኑት የአንደኛ እና የሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ወደ ተግባር በመግባት የሒሳብ አያያዙን ሥራ በዘመናዊ የሒሳብ አሠራር መሠረት ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ በ3ኛው እና በመጨረሻው ዙር የሠለጠኑ ሠልጣኝ የሒሳብ ሠራተኞች ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት ጀምሮ በተሰጣቸው ስልጠና መሠረት የሒሳብ አያያዙን ሥራ በዘመናዊ የሒሳብ አሠራር መሠረት እንደሚሠሩ ተጠቁሟል፡፡  
በመሆኑም አሁን እየተሰጠ ያለው የዘመናዊ የሒሳብ አያያዝ ሙያ ስልጠና እንደተጠናቀቀ በተመሳሳዩ የቁጥጥር ሠራተኞች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና እንደሚቀጥል የሀገረ ስብከቱ  የቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍል አብራርቷል፡፡
ስለሆነም ሀገረ ስብከቱ ይህንን መልካም ተሞክሮ አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል፤ የገዳማቱና የአድባራቱ ሠራተኞችም ትኩረት ሰጥተው ሥልጠናውን በተሻለ ንቃትና ትጋት ሊቀጥሉበት ይገባል እንላለን፡፡
 

 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን ቅዱስ ሲኖዶስ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የሞት አደጋ አስመልክቶ የሀዘን መግለጫ አስተላለፈ

pp009

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የሞት አደጋ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ
የሀዘን መግለጫ ፡፡
መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ ድንገተኛ የሞት አደጋ ደርሷል ፡፡ በደረሰውም አሳዛኝ አደጋ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር አምላካችን በደረሰው ሕልፈተ ሕይወት ለተጎዱ ወገኖች ቤተሰቦች መጽናናትን፣ ብርታትን እንዲሰጥልን፤ የሟቾቹንም ነፍሳት በመንግሥቱ እንዲቀበልልን በመጸለይ የተሰማንን ኀዘን እየገለፅን፣ ለእነዚሁ በድንገተኛ አደጋ ለተለዩ ወገኖቻችን ከመጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግላቸው፤ እንዲሁም ቤታቸው በመፍረሱ ምክንያት በመጠለያ ለሚገኙ ወገኖቻችን ከቤተ ክርስቲያናችን ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ርዳታ እንዲሰጥ ቋሚ ሲኖዶስ ወስኗል ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 8 ከ 104

አድራሻ

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ኢ-ሜይል: aadioces@gmail.com

ድረ ገጹ ውስጥ ይፈልጉ

ሀሳበ ባሕር(የዘመን ቁጥር)

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ግጻዌ