መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ጽጌ ቅድስ ኡራኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ኃይል ራጉኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/590538kidste_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/895720giorgis.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/903816bole_medhaniealem.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/683566trinity.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/821897entoto_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/310283meskaye_1.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/904160BEATA_MARIAM.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/578084urael.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/812647gebrie_gedam.jpg http://www.addisababa.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/681179raguel.jpg
በዓለ ሆሳዕና እና ታሪኩ

            እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ!!

002

የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም “ በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና  ከረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል።

 በዚሁ በዓለ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርአየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካሪያስ እንደተነገረው ‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ ዘካ.9፣9። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናግሮ ነበር።

ሲመጣም ‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።’’ በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። 2ኛ ነገ. 9፣13 ። የሆሣዕና በዓል በቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡርክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ መዝ.117፣26 በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ታድላለች ። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚመለከቱ የቅዱስ ማቴዎስ (ማቴ. 21፣1-17)፤ የቅዱስ ማርቆስ፣(ማር.11፣1-10)፤ የቅዱስ ሉቃስና (ሉቃ.19፣29-38)፤ የቅዱስ ዮሐንስ (ዮሐ.12፣12-15) ወንጌላት ይነበባሉ ።

ታዲያ አኛ ይህን ዐቢይ በዓል የምናከብረው እንዴት ነው? በነቢያቱ ከላይ እንደተገለጠው በወንጌላቱም እንደተፈጸመው እርሱ ወደ እኛ የሚመጣበት ጊዜ መቼ ነው? ሲመጣስ ምን እናድርግ? የእግዚአብሔርን መምጫ ጊዜ ማሰብና መዘጋጀት ያለብን እንዴት ነው? ምክንያቱም በዓሉ ከምንም በላይ የሚጠቅመን ለእኛ ነውና ። ስለዚህ ይህን በዓል ስናከብር ሰላምንና ፍቅርን የእርሱን የክብር አመጣጥ እያሰብን ልንተገብረው ይገባል። ለጌታ የማያስፈልግ ፍጥረት የለም ይልቁንም የክብር ዘውድ አድርጎ በመልኩ የፈጠረው ሰው ያስፈልገዋል።ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጠረ ማንም የለም።እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ዓላማና ዕቅድ የተፈጠርን እንደመሆናችን መጠን እግዚአብሔር የሚከብርበትን ሥራ ልንሠራ ይገባል።አህያ በሰው ሰውኛ ሲታይ የንቀትና የውርደት ሊመስል ይችላል ።የአህያን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት ግን

  1. በለዓም በሥጋዊ ገንዘብ መንፈሳዊ ዓይኑ ታውሮ እግዚአብሔር ያልረገማቸውን እስራኤላውያንን ሊራገም ሲሄድ እስራኤላውያንን እንዳይራገም ለመንገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው መልአክ በሚሄድበት መንገድ ላይ ቆሞ ሳለ ከበለዓም ይልቅ ያየችው የበለዓም አህያ ነበረች ። አህያይቱም መልአኩን አክብራ መንገዱን እንደለቀቀችለት ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ዘኅ.22፣23።
  2.  በትንቢተ ኢሳያስ 1፣3 ‘ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጪ በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ እሥራኤል ግን አላወቀም’’ እንደተባለው ጌታ በተወለደ ጊዜ ትንቢቱን ምሳሌውን የሚያውቁ እሥራኤላውያን ባላወቁ ባለተቀበሉ ሰዓት በዚያ በብርድ ወራት እናቱ የምታለብሰው ልብስ አጥታ ቅጠል አልብሳው በነበረ ጊዜ ለጌታ ሙቀት የገበሩለት እረኞቻቸውን ተከትለው የመጡ ከበቶች ላሞችና አህዮች ናቸው። ‘ወአስተማወቅዎ አድግ ወላህም’’ እንዲል አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም።።
  3.  በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም ለከብር የተሸከመችው አህያ ናት። ጌታን የተሸከመችው አህያ ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጉላታል። አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ እንደበድባት ነበር፡ ነውም። ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ።

ስለዚህ ክርስቶስ በአህያይቱ ላይ እንዲቀመጥባት ልብስም እንደ ተጎዘጎዘላት እኛም ጌታ በፀጋውና በረድኤቱ እንዲያድርብን ልባችንን ከኃጢአትና ከተንኮል አንጽተን ፍቅርንና ትሕትና ልንጎዘጎዝ ይገባል።

ጌታ በኛ ላይ በፀጋው ሲያድር በእርሱና በቅዱሳኑ ዘንድ ያለን ክብርና ፀጋ ታላቅ ነው። በነገር ሁሉ መከናወን ይሆንልናል።ክርስቶስን በመሸከሟ የአህያይቱ ታሪክ እንደተለወጠ ሁሉ በክርስቶስ ማደሪያነታችን ያለፈው መጥፎ ታሪካችን ይለወጣል።እንግዲህ በእለተ ሆሣዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ በዝማሬ እንደ ንጉሰ እንደተቀበሉት እኛም ሀሴትን አድርገን ‘ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት…’’ በማለት እናመሰግናለን።

              ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን።

ታድላለች

 
በሃይማኖት ሽፋን ቅ/ኤልያስ መጥቷል ብለው በኤልያስ ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ንፁሀን ዜጎችን ሲያስደበድቡና ሁከት ሲፈጥሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታሰሩ

ቀደም ሲል በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች የተፃፉትን ጽሑፎች በአህጉረ ስብከታችን ዌብ ሳይት ስናስነብብ መቆየታችን አይዘነጋም፡፡ ምንም እንኳን ጉዳዩ ዘግይቶ በተለያዩ ሚዲያዎች መሰራጨት የጀመረ ቢሆንም ቀደም ሲል ከሁለት ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጀርባ በተለምዶ ቆሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መንደር ቤተክርስቲያኑንና ህብረተሰቡን ሲረብሹ የቆዩ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤት ጉዳዩን እየባሰ ሲሄድ በመስከረም ወር 2ዐዐ5 ዓ.ም ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ክስ መስርቶ በፍ/ቤት ትእዛዝ ግለሰቦቹ ከተከራዩት ቤት እንዲወጡና አከራዮችም ተከራዮቹ በአስቸኳይ እንዲያስወጡ ውሳኔ ተወስኖ ነበር፡፡

ይሁንና ግን በአፈፃፀም ሂደት የሚመለከታቸው አካላት እስከ አሁን ድረስ እልባት ባለማግኘቱ ካቴድራሉንና በካቴድራሉ ጀርባ ያሉ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡ ግለሰቦቹ መኖሪያ ቤታቸው የት እንደሆነ በእርግጠኛነት ማወቅ ባይቻልም ሁሉም የሚገናኙት ከሥላሴ ጀርባ በተከራዩት ቤት ነው የመገናኛ ሰዓታቸውም ከቀኑ በ11 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡3ዐ ነው፡፡ የተከራዩት ቤት መጠኗ አነስተኛ ብትሆንም እስከ 4ዐዐ የሚደርሱ ሰዎች ኃይማኖትን ይሁን ፖለቲካ፣ እብደት ይሁን ስካር ባልታወቀ ሁኔታ ከበሮ እየመቱ እጣን እያጨሱና መጠጥ እየጠጡ እንደሚያመሹ የሰፈሩ ሰዎች በግልጽ ከመናገራቸውም በላይ ከቅዳሜ በስተቀር ሁልጊዜ እዛው ቦታ ላይ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቤቱ ጎን ያሉ ነዋሪዎች ማለፍ አትችሉም፣ ጫማችሁን አውልቁ ወዘተ እያሉ በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን በሰላም የመኖር መብት ሲያሳጧቸው የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ ይባስ ብሎ በ15/ዐ8/2ዐዐ5 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡3ዐ ላይ እንደ ሰፈሩ ሰዎች አባባል ቁጥራቸው ከ5ዐ - 1ዐዐ የሚሆኑ በሰፈሩ ሰዎች ላይ ለማድረስ ጀምረውት የነበረውን የድብደባ ጥቃት በአካባቢ ባሉት የፖሊስና የመከላከያ ኃይል አማካይነት ጉዳቱ ሊቀንስ ቢችልም በዚሁ ዕለት ጉዳዩን በዋናነት ሲመሩ የተገኙት (የነበሩት)እጅ ከፍንጅ ተይዘው 4 ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡

ቦታው ድረስ በአካል ሄደን ለማረጋገጥ እንደቻልነው 3 ሰዎች ተመትተው እቤታቸው ተኝተው አይተናል፡፡ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ቦታው ድረስ በመሄድ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እያደረጉ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤትም ከአሁን ቀደም ከቤቱ እንዲወጡ ፍ/ቤቱ የወሰነበትን ውሳኔ አያይዞ ለፖሊስ ጣቢያው ልኳል፡፡

የአካባቢው ማኀበረሰብም ፖሊስ ጣቢያው ድረስ በመሄድ ለዓመታት በዚሁ ችግር ሲኖሩ መቆየታቸውንና አሁን የደረሰባቸውን ችግር ገልፀው ክስ መስርተውባቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የቤተክርስቲኒቷን ስም በማጥፋታቸው በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡

 
የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

4
መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መልዕክት

ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የስብከተ ወንጌልን እንቅስቃሴ አስመል ክተው ለኆኅተ ጥበብ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሙሉ ማብራሪያውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

“ማዕረሩሰ ብዙኀ ወገባሩ ኀዳጥ ሰአልዎ እንከ ለበዓለ ማዕረር ከመ ይዌስክ ገባረ ለማዕረሩ” መከሩ ብዙ ነው ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው እንግዲህ ለመከሩ ሠራተ ኞችን ይጨምር ዘንድ ባለመከሩን ለምኑት /ሉቃ. 10÷2) ለአንድ ባለ አዝመራ ግለሰብ የሚያ ርስ፣ የሚዘራ፣ የተክል፣ የሚኮተኩት፣ የሚያርም፣ ከአራዊት የሚጠብቅ፣ ፍሬውን የሚለቅም /የሚያጭድ የሚወቃ) እንደሚያስፈልገው ሁሉ፡ የእግዚአብሔር አዝመራም እንዲሁ የምእመናንን ልብ በወንጌል የሚያለሰልስ፣ የሚያስተምር፣ የሚያጠምቅ ሕዝብን አሕዛብን ህያዋንና ሙታንን የሚያገለግል ከገቢረ ኃጢአት ጠብቆ ወደ ገቢረ ጽድቅ የሚመልስ ከመጨረሻው ግብ ለንስሐና ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ አብቅቶ የመንግሥተ ሰማያት ዜጎች የሚያደርጉ፣ የቤተ እግዚ አብሔር መገልገያ የሚሆኑ ንዋያተ ቤተ መቅደስን ሀብትና ንብረትን ዐፀደ ቤተ እግዚአብሔርን ቅጽረ ቤተክርስቲያንን የሚሰበስብ፣ የሚጠብቅ፣ የሚያስጠብቅ፣ የሚያስተዳድር፣ የሚያስተነትን እውነተኛ የእግዚአብሔር አዝመራ ሰብሳቢ ጠባቂ ሠራተኛ ያስፈልጋል፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ኃይለ ቃል እንደተ ገለጸው የዚህ ዓለም አዝመራ ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ማርያም ተገልጦ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጠብ መጋረጃ ለመግለጥ ወደዚህ ዓለም በመጣበት ጊዜ በመዋዕለ ትምህርቱ ከላይ በተጠቀሰው ኃይለ ቃል መከሩ ካህናት ምእመናን ምእመናት ወጣቶች እየበዙ የመከሩ ሠራተኞች ሐዋርያት ካህናት ጻድቃን ሰማዕታት ባነሱበት በመጀመሪያው የክርስትና ዘመን መከር አምላካችን ለብዙ ጊዜ የመከሩ ሠራተኞች እንዳያንሱ ራሱን የመከሩን ባለቤት የታመኑ ሐዋርያትን ካህናትን ልዩ ልዩ ሠራተ ኞችን በየዘመኑ ይሰጥ ዘንድ መለመን እንደሚገባ ለማረጋገጥ ነው፡፡

ወንጌላዊ ቅ/ሉቃስ የጻፈው ቢሆንም ሀሳቡ የእግዚአብሔር መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ወቅት ድርጊት የተነገረ ሳይሆን ዛሬም ቢሆን በገጠር በከተማ በበረሀ በደጋ የእግዚአብሔር መከሩ ብዙ ነውና ይህንን መከር የሚሰ በስብ ሰራተኛ ዛሬም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዘመናችን የአሠራር መርህ ከላይ እስከ ታች ከታች እስከ ላይራሱን የመከሩን ባለቤት የታመኑ ሐዋርያትን ካህናትን ልዩ ልዩ ሠራተ ኞችን በየዘመኑ ይሰጥ ዘንድ መለመን እንደሚገባ ለማረጋገጥ ነው፡፡ ወንጌላዊ ቅ/ሉቃስ የጻፈው ቢሆንም ሀሳቡ የእግዚአብሔር መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ወቅት ድርጊት የተነገረ ሳይሆን ዛሬም ቢሆን በገጠር በከተማ በበረሀ በደጋ የእግዚአብሔር መከሩ ብዙ ነውና ይህንን መከር የሚሰ በስብ ሰራተኛ ዛሬም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዘመናችን የአሠራር መርህ ከላይ እስከ ታች ከታች እስከ ላይ በተዘረጋው መዋቅር /ከመንበረ ፓትር ያርክ እስከ አጥቢያ፣ ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ የተሰማራ የእዚአ ብሔር ሠራዊት የእግዚአብሔርን አዝመራ ለመጠበቅ ለማስጠበቅ ቀን ከሌሊት ተግተው በየሥራ ዘርፉ ተሰል ፈዋል፡፡

የአዝመራውን አዘገጃጀት ለማሳ መር ነው ቅ/ሲኖዶሰ በቅርቡ አዲስ አበባን በ4 አህጉረ ስብከት እንዲዋቀር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የወሰነው፣ የመዲናችን አንዱ ማእዘን ሰሜን አዲስ አበባ ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ሲፈቀድ፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ 13 የመምሪያ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በድምሩ 24 ገባረ ማዕረር ተሠልፈዋል፡፡ መከሩ እንደ መብዛቱ መጠን በባለ መከሩ በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አዲስ አበባን በ4/አራት/ አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ሲወስን ከአራቱ አንዱ 25 አብያተ ቤተክርስቲያናትን ያቀፈውን የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው፡፡

የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል እና ማቴርያል አደረጃጀትን በተመለከተ

ከላይ እንደገለጥነው በ24 የሰው ኃይል፣ በቀድሞው ሕንጻ በ10 ቢሮ፣ በ2 ተሽከርካሪና ሹፌሮች፣ በ3 ኮምፒውተር ከሌሎቹ አህጉረ ስብከት ጋር በጋራ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌፎን አግልገሎት ተደራጅቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ በልማት የነበሩ የልማት ተቋማት ተደራ ጅተው እንዲቀጥሉ በሰው ኃይል ልማት የተለያዩ የግንዛቤ መልእክቶች ተላል ፈዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በተመለከተ

ቤተክርስቲያኗ ከክርስቶስ በተቀ በለችው አደራ መሠረት የሰው ልጆች የዘር፣ የቀለም፣ የጎሳ፣ የሀብት ልዩነት ሳይደ ረግባቸው በእኩልነት መንፈስ በፍትሐዊ መንገድ “ወይኩን ነገርክሙ እመኒ እወ ወእመኒ አልቦ” ነገራችሁ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ደግሞ ሐሰት ማለት ይሁን እንደተባለው ሕግና መመሪያ የሚፈቅደውን በአጭር ሰዓት መፍትሔ መስጠት ሕግና መመሪያ የማይፈቅደውን በማስገንዘብ መልስ መስጠት በመቻሉ በውይይት ፍትሐዊ አሠራር እንዲነግሥና በሀ/ስ/ፍጹም ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ለማድረግ ተችሏል፡፡ ለአብነት በመንበረ መንግስት ቅ/ ገብርኤል ገዳም፣ በእንጦጦ ደ/ኃ/ቅ/ ራጉኤል ቤተክርስቲያን የነበረውን ችግ ርና የተሰጠውን አመርቂ ስልታዊ መፍትሔ መጥቀ ስ ይቻላል፡፡

ሐዋርያዊ አግልገሎትን በተመለከተ

በሀገረ ስብከቱ በአዲስ አበባ በቀደም ትነታቸው በታሪካዊነታቸው የሚጠቀሱ ገዳማትና አድባራት የሚገኙበት ከመሆኑ አንጻር እስከአሁን በዘወትር ከሚሠሩ የወንጌል አገልግሎት በተጨማሪ ቀደም ሲል በብዙ ምዕናን ዘንድ አድናቆትን አትርፎ የነበረውና በመሀል ተቋርጦ የነበረው የስብከተ ወንጌል የአንድነት ጉባዔ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

በወር 3 ጊዜና በዓመታዊ በዓላት በጥም ቀትና በመሳሰሉ በዓላት በቤተክርስቲያኑ ከሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት በተ ጨማሪ እጅግ ትልቅ ትርጉም ሊሰጠው የሚችል የወንጌል አግልግሎት ለምእ መናን ለማድረስ ተችሏል፡፡

ያጋጠሙ ችግሮች

የሥራና ሠራተኛ አለመገናኘት፣ የበጀት በማዕከል መያዝና ሥራዎችን በተገ ቢው ቅልጥፍና ለማከናወን አለመቻል፣ የቢሮ እጥረት፣ የቢሮ ፈርኒቸርና ኮምፒ ውተር ችግር ዋና ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የወደፊት ዕቅድ

  1.   ሐዋርያው ቅ/ያዕቆብ በመልእክቱ እግዚ አብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ይህንና ያንን እናደርጋለን እንዳለ ያዕ.4÷15
  2.  እግዚአብሔር ወዶና ፈቅዶ በሰጠን ጊዜ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዲ ፈቱ ጥረት ማድረግ፣
  3.  በቅጥርና ዕድገት ዙሪያ ኮሚቴ በማቋ ቋም የቅጥር ሥራ በውድድር እንዲ ከናወን ማድረግ፣
  4. ለአስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ግን ባታ ሥልጠና መስጠት፣ ለሰባክያንና ለካህናት ሥልጠና በመስጠት የሰለጠነ የሰው ኃይል ክፍተትን መሙላት፣
  5. የባለ ጉዳይ የመስተንግዶ ቀን በመ ወሰን ተገቢውን መስተንግዶ መስጠት፡፡

በልማት

በየአድባራቱ የተጀመሩ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮግራሞች እንዲፈጸሙ አዳዲስ የልማት አውታሮች በየዘርፉ እንዲሠሩ በሀገረ ስብከቱ ቢሮ የተጠና ልማት እንዲጀመር ማድረግ በማለት የሀገረ ስብ ከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አብራርተዋል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም በበኩሉ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደነቀ ሁሉም የዚህ ልማታዊ እንቅስቃሴ ተፎ ካካሪ በመሆን የየራሱን የሥራ ውጤት ለያስመዘግብ ይገባል እንላለን፡፡

ምንጭ ኆኅተ ጥበብ መጽሔት

 
<< ጀምር < ወደኋላ 91 92 93 94 95 96 97 98 99 100 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 100 ከ 109

አድራሻ

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ኢ-ሜይል: aadioces@gmail.com

ድረ ገጹ ውስጥ ይፈልጉ

ሀሳበ ባሕር(የዘመን ቁጥር)

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ግጻዌ